የወልድ ዋሕድ ሰ/ት/ቤት የርቀት ትምህርት ተማሪዎች ትምህርታዊ የጉዞ መርሐ ግብር ተካሔደ ።
ሐምሌ 27 2017 ዓ.ም – ወልድ ዋሕድ ሚዲያ
በኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተክርስቲያን የወልድ ዋሕድ ሰ/ት/ቤት የርቀት ክፍል አዘጋጅነት ከአዲስ አበባ በ50 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደ ሚገኘው ገዋሳ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና አቡነ ሀብተማርያም ቤተክርስትያን ልዩ የአንድነት ጉዞ መርሐ ግብር ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም ተካሒዷል ።
በዕለቱም የተለያዩ መርሐ ግብራት የቀረቡ ሲሆን የዋሻ ጉብኝት፣ መርሐ-ግብራችን ተጀመረ የመክፈቻ ዝማሬ በሕብረት ከዘመርን በኋላ የሕብረት ማዕድ ተጋራን በማስከተልም ቃለ እግዚአብሔር በ ዲ/ን እስጢፋኖስ ደሳለኝ ተሰጥቷል በመቀጠልም ዘማሪ መብዓ ጽዮን ዝማሬ ከቀረበ በኋላ የጥያቄዎቻችሁ መልሶች በሚል መርሐ ግብር በመጋቢ ሐዲስ ሐብተማርያም ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል በመጨረሻ በመልዓከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረማርያም በጸሎት ተጠናቋል ።
በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ 400 የርቀት ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
በነገሮች ሁሉ የረዳን አምላከ ቅዱሳን ይክበር ይመስገን




