X
የደብራችን የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተ-ክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰ/ት/ቤት ከደብሩ ከተመሠረተበት ሐምሌ 22 ቀን 1,976 ከወራት በፊት ለደብሩ የሰ/ት/ቤት አገልግሎት እና የደብሩ ምሥረታ ክብረ በዓል አከባበር መንፈሳዊ ዓላማ ባነገቡ ጥቂት ወጣቶች እና አገልጋይ ካህናት ፣ ዲያቆናት አማካኝነት በ1,976 ግንቦት ወር ተመሠረተ።

Contact Info

የትምህርት እና ሥልጠና ክፍል

Weld Wahed > የትምህርት እና ሥልጠና ክፍል
    1. ተከታታይ የኮርስ መርሃ ግብር
    • የቀዳማይ ፤ የካልዓይ ፤ የሳልሣይ እንዲሁም የራብዓይ ኮርሶችን በተከታታይ በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰጣል፡፡ ዘወትር ቅዳሜ እና እሁድ ከ 11፡30 – 1፡30
    1. ሳምንታዊ የወጣቶች ጉባኤ
    • ዘወትር ረቡዕ ከ 12፡00 – 1፡30 “የሕይወት ማዕድ” የተሰኘ የቃለ እግዚአብሔር ምግብ የሚዘጋጅበት መድረክ ነው፡፡
    1. የርቀት ትምህርት
    • በጊዜ ጥበት እና በሥራ መደራረብ ምክንያት መደበኛውን የኮርስ መርሐ ግብር መከታተል ላልቻሉ ምእመናን በወር አንድ ቀን እየተገኙ የሚማሩበት የትምህርት መርሐ ግብር ሲሆን ትምህርቱ ለአንድ ዓመት በቋሚነት የሚሰጥ ነው፡፡
    1. የአብነት ትምህርት
    • በአብነት ትምህርት ቤት ሥርዓት በተዋረድ ቋሚ የትምህርት መርሃ ግብር በበጋ እና በክረምት ዘወትር ከሰኞ – አርብ ከ11፡00 – 1፡30 ይሰጣል፡፡
    1. የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎቶች
    • ዘወትር ከሰኞ – አርብ ከ11፡00 – 1፡30 እንዲሁም ዘወትር ቅዳሜ እና እሁድ ከጠዋት 3፡00 – 2፡00 ሰዓት ድረስ ለአገልግሎት ክፍት ነው፡፡
    1. መንፈሳዊ ሥልጠና ዝግጅት
    • የአገልግሎት ሥልጠና
    • የካህናት ሥልጠና
    • የዲያቆናት ሥልጠና
    • የተግባራዊ አገልግሎት ሥልጠና
    • የአመራር ሥልጠና
    • የንዑሳን ሥልጠና
    • ሙያዊ ሥልጠና
    • ፎቶ እና ኤዲቲንግ ሥልጠና
    • የቅድመ ጋብቻ ሥልጠና
    • የተተኪ መምህራን ሥልጠና
    • የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ሥልጠና