የወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት ዓርማ ስያሜዎች እና ትርጉማቸው
- በመጀመሪያ በነጭ የተገለጸው የተከፈተ መጽሐፍን ያሳያል፡፡ የተከፈተ መጸሐፍ ዕውቀትን ፣ ጥበብን ፣ መማርን እና ማስተማርን ይወክላል፡፡ ሰንበት ትምርት ቤታችን ቃለ እግዚአብሔርን የምንማርበት መሆኑን እና በዕወቀት ላይ የተመሠረተን እምነትን አንዲሁም በእምነት ላይ የተመሠረተ አገልግሎት አንዳለን ያሳያል፡፡
- ከመጽሐፉ በላይ የሚገኘው የምናገለግልበትን የደብራችንን የመካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ሕንፃ ቤተክርስቲያን የሚያሳይ ሲሆን በተጨማሪም ቤተክርስቲያን በኅብረት ተሰብስበን የምናመልክበት የአንድነት ስፍራ መሆኑን ያመለክታል፡፡
- በስተምሥራቅ በኩል የሚገኘው የስንዴና የወይን ፍሬ ሲሆን በቤተ ክርስቲያናችን ትልቁ ምሥጢር የሆነውን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱስ ሥጋው እና የክቡር ደሙ ምሳሌ ሲሆን አገልጋይ ሰንበት ተማሪዎች በዚህ ምሥጢር ውስጥ ታሳታፊ መሆናቸውን ለማሳየት ነው፡፡
- በስተምዕራብ በኩል የሚገኘው ንዋያተ ቅድሳት ደግሞ በዝማሬ የምንገለገልባቸውን መሣሪያዎች ያየዘ ነው፡፡
- ሁለቱም አንድ ላይ ሲሆን ሰንበት ትምህርት ቤታችን ቤተክርስቲያንን ከቤተልሔም አንሥቶ እስከ ዐውደ ምሕረት ፣ ከውስጥ አንሥቶ እስከ ውጪ የሚያውቃት ፣ ምሥጢሯን የሚካፈል ፣ የሚያገለግላት ፣ የቅዱስ ያሬድን ልቡና የያዘ ትውልድ የሚፈራባት ቦታ መሆኗን ለማሳየት ነው፡፡
- ዓርማው ክብ መሆኑ አንድነትን፣ መዋደድን ፣ እርስ በርስ መደጋገፍን ፣ መተሳሰብን ፣ ሕብረትን ያመለክታል
- “ወውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ” የሚለው በየሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1፤14 ላይ የሚገኘው ኃይለ ቃል ሲሆን የቤተክርስቲያናችን የዕምነት መሰረት የሆነውን ተዋህዶ የሚለውን ቃል የሚያመላክት ነው አንድም “ወልድ ዋህድ” የተሰኘውን የሰንበት ትምህርት ቤታችንን ስያሜ የሚገልጽ ሐሳብን የያዘ ነው፡፡
- የዓርማውን ቀለም በተመለከተ በዓርማው ዙሪያ የሚገኙት አረንጓዴ ፤ ቢጫ እና ቀይ ቀለሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ፣ ሥርዓት ፣ ዶግማ እና ቀኖና የተመሠረተ ኅብረት እንዳለን ያመለክታል
- የአርማው መደብ የሆነው አረንጓዴ ቀለም ሕይወትን ፣ በእግዚአብሔር ቤት ያለ የህይወት መታደስን ፣ ተፈጥሮን ፣ ልምላሜን የሚገልጽ ሲሆን ብርቱካናማው ደግሞ የደስታ መግለጫ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቤት ያለ ደስታን እና መንፈሳዊ ሙቀትን ይገልጻል፡፡
- 1976 ዓ.ም የሚለው ሰንበት ትምህርት ቤታችን የተመሰረተችበትን ዕድሜ ይገልጻል፡፡