የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና የሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የደረሰውን አደጋ ተመለከቱ።
(#EOTCTV ነሐሴ ፫ ፳፻፲፯ ዓ.ም)
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና የሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ሰሞኑን በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ሳቢያ በሕንጻ ቤተክርስቲያኑና በዕቃ ቤቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ።
በጉብኝቱ ላይ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ የተገኙ ሲሆን በአደጋው ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እንዳሉት በደረሰው አደጋ ምክንያት ሕንጸ ቤተክርስቲያኑን ለመጠገን የሚደረገውን ጥረት አድንቀው የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪና የሥራ ኃላፊዎቹ ሕዝበ ክርስቲያኑን በማስተባበር እያደረጉት ያለውን ጥረት አጠናክረው በመቀጠል ቀሪ ሥራዎቸን በአስቸኳይ ለማከናወን ይቻል ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑ የጀመረውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
©ኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ


