X
የደብራችን የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተ-ክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰ/ት/ቤት ከደብሩ ከተመሠረተበት ሐምሌ 22 ቀን 1,976 ከወራት በፊት ለደብሩ የሰ/ት/ቤት አገልግሎት እና የደብሩ ምሥረታ ክብረ በዓል አከባበር መንፈሳዊ ዓላማ ባነገቡ ጥቂት ወጣቶች እና አገልጋይ ካህናት ፣ ዲያቆናት አማካኝነት በ1,976 ግንቦት ወር ተመሠረተ።

Contact Info

Faq

Weld Wahed > Faq
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ተጠብቆ ሳይለወጥ ሳይበረዝ ከትውልድ ወደ   ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ:: ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ የሆነ ምእመን የሃይማኖቱን ሥርዓት  በውል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ:: ወጣቶች የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት ተምረው ወላጆቻቸውንና ታላላቆቻቸውን አክባሪ ለሀገርና ለወገንም መልካም ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ:: "በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ" የሚለውን የአምላክ ትእዛዝ ወጣቶች እንዲፈጽሙ ማስቻል:: (መክ. ፲፪፡፩)
በሰንበት ትምህርት ቤታችን ሃይማኖት ከምግባር አጣምረው የያዙ አባላትን ማፍራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ተጠብቆ ሳይበረዝ እና ሳይለወጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ፡፡ ሕፃናት እንዲሁም ወጣቶች በሰ/ት/ቤቱ ተደራጅተው እየተማሩ የቤተክርስቲያንንም ሆነ የሀገርን ታሪክ በሚገባ አውቀው በነገረ-መለኮት እና ሃይማኖታዊ ትምህርት ብስለት እንዲያገኙ የነገዋን ቤተክርስቲያንና ሀገርን በኃላፊነት ለመረከብ ብቁዎች እንዲሆኑ ማድረግ ሕፃናትና ወጣቶች የቤተክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት (ቃለ እግዚአብሔር) ተምረው ወላጆቻቸውን እና ታላላቆቻቸውን አክባሪዎች እንዲሆኑ፤ በአጠቃላይ በሃይማኖት እና በሥነ-ምግባር ታንጸው እንዲያድጉና ለሀገርና ለወገን መልካም ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ ሕፃናትና ወጣቶች ወደ ቤተ-እግዚአብሔር እንዲመጡና በጉብዝናቸው ወራት ፈጣሪያቸውን እንዲያስቡ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን ለመፈጸም እንዲችሉ ማድረግ የሰ/ት/ቤቱ አባላት ያላቸውን ሙያ፤ ዕውቀት፤ ገንዘብና ጉልበት ለቤተክርስቲያኒቱ እንዲያበረክቱ ማድረግ ነው፡፡  
መንፈሳዊነት፣ አንድነት፣ መደጋገፍ ፣ ቀጣይነት፣ አገልጋይነት ክርስቲያናዊ ኃላፊነት፣ ጽናትና ምስክርነት በፍቅር የተሞላ አገልግሎት

    Fill The Contact Form
    Feel free to contact with us, we don’t spam your email
    01

    "ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ"

    "አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር ! ሁልጊዜ ተማር ! ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር! ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ ። ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፡፡ ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለህ፡፡ ይህች የንስሐ በር ትሆንልሃለች፡፡ አንድ ቀንም ወደ ንስሐ ትመራሃለች !!!
    02

    ይስሐቅ ግብፃዊ

    ከሞተ በኋላ ስለሚኖረው ዕውቀት በመጨነቅ ራስህን  አታታል። በዚህ ዓለም የዘራኸውን በሚቀጥለው ዓለም እንደምታጭድ እወቅ። ከዚህ ዓለም ሰው ከተወሰደ በኋላ ሥራ የሚሠራበት  ሌላ ዓለም የለም ዋጋ የሚከፈልበት እንጂ። ሥራው ያለው እዚህ ነው፤ ሽልማት እዚያ ነው። ትግሉ እዚህ ነው ፤  የድል አክሊሉ እዚያ ነው።
    03

    ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ

    "ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን"
    04

    ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ

    "ድሀ በቤትህ ደጃፍ ይጮኻልን? ተነሥተህ በደስታ የቤትህን ደጅ ክፈትለት ፤ የድኃውን ልመና ቸል አትበል፡፡ በነፍሱ የመረረው ነውና ቢረግምህ እግዚአብሔር አቤቱታውን ይሰማዋል፡፡ ስለዚህ ይረግምህ ዘንድ ምክንያት አትሁነው ፤ አዝኖ ከሆነ በመልካም መስተንግዶ ደስ አሰኘው፡፡ በኀዘን የከበደው ልቡ በአንተ ይረፍ፤ በሕይወት ዘመንህ ማጣት የሚያመጣቸውን ሥቃዮች ታውቃቸዋለህና ችግረኛውን ከቤትህ ደጅ አትመልሰው፡፡"

    ዜናዎች

    “ስለ ምን ጾምን?” (ኢሳ.፶፰፥፫)

    “ስለ ምን ጾምን?” (ኢሳ.፶፰፥፫) መምህር ዮሴፍ በቀለ ጥር ፴፤፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት የነነዌ ከተማ ሰዎች ኃጢአት በትንቢተ ዮናስ…
    Read Details

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጀልባ…

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጀልባ መገልበጥ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች አስመልክቶ የተሰማውን ኀዘን…
    Read Details

    ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓል ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ…

    ሐምሌ ፲፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ዓ.ም++++++++++++++++++ቁልቢ -ምሥራቅ ሐረርጌ"""""""""""""""""""""""""""""""ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓል ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ…
    Read Details

    .